Employer: Inayaz construction
Location: bole, Addis Ababa
Job type: Full-time
Work arrangement: On-site
Application deadline: 2026-11-07
የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ ኢናያዝ ኮንስትራክሽን እና ማቴሪያል ኢምፖርት እና ኤክስፖርት ቀልጣፋ፣ ንቁ እና ከፍተኛ የማደራጀት ብቃት ያለው የጉዳይ አስፈፃሚ በቋሚነት አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል። ይህ የሥራ መደብ በቢሮ ውስጥ የደንበኞችን መረጃ እና የድርጅቱን ጉዳዮች የማስተዳደር፣ እንዲሁም በውጭ ያሉ የመንግሥትና የግል ተቋማት ጉዳዮችን አጣጥሞ የመስራት ኃላፊነትን ያካትታል። ዋና ዋና የሥራ ኃላፊነቶች፦ ተቋማዊ ግንኙነት፦ በድርጅቱና በተለያዩ የመንግሥት/የግል ተቋማት (እንደ ገቢዎች፣ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ባንኮች፣ ወዘተ) መካከል ያሉ ጉዳዮችን በቅርበት መከታተልና ማስፈጸም።
ሰነዶችና ፈቃዶች፦ የንግድ ፈቃድ ማደስ፣ የግብርና ታክስ ፋይሎችን ማስተካከል እና ተያያዥ ጉዳዮችን መፈጸም።
ክፍያዎችን ማስተናገድ፦ የድርጅቱን የውሃ፣ መብራት፣ ስልክ እና ሌሎች መሠረታዊ ክፍያዎችን በወቅቱ መፈጸም።
የባንክ ሥራዎች፦ በባንክ በኩል የሚከናወኑ የገንዘብ ማስገባት፣ የሰነዶች ማድረስና መቀበል ሥራዎችን በኃላፊነት ማከናወን።
ተፈላጊ መስፈርቶች፦ የትምህርት ደረጃ፦ በማኔጅመንት፣ በሕግ፣ በአስተዳደር ወይም በተዛማጅ መስኮች ዲፕሎማ ወይም ሰርተፊኬት ያለው።
የሥራ ልምድ፦ ከ 2 እስከ 4 ዓመት በጉዳይ አስፈጻሚነት (Liaison Officer) የሠራ (ይመረጣል)።
ፆታ፦ ወንድ
የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ፣ ቦሌ (Bole)
የሚያስፈልጉ ክህሎቶችና ስብዕና፦ ክህሎት፦ ከፍተኛ ንቁነት፣ መልካም የኮሚዩኒኬሽን ችሎታ እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር የመደራደር/የማስፈጸም ብቃት።
ታማኝነት፦ ሙሉ በሙሉ የታመነ፣ በስነ-ምግባሩ ምስጉን እና የጠራ ስም ያለው።
ቅልጥፍና፦ ያለምንም ማስታወሻ እና ማሳሰቢያ የተሰጡ ትእዛዞችን በፍጥነት እና በሰዓቱ የመፈጸም አቅም ያለው።
የቴክኖሎጂ እውቀት፦ በኤክሴል (Microsoft Excel)፣ በሞባይል ባንኪንግ (ቴሌብር / CBE Birr) እና በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ በቂ እውቀት ያለው።
የቋንቋ ችሎታ፦ በአማርኛ ቋንቋ ጥሩ የጽሁፍ እና የንግግር ችሎታ ያለው (መሰረታዊ የእንግሊዝኛ እውቀት ያለው ይመረጣል)።
Requirements: Brokerage & Case Closing, Time Awareness, Communication
Skills and tags: Brokerage & Case Closing, Time Awareness, Communication
Apply for this job
Source: Afriwork