Employer: Haylo Ethio Trading PLC
Location: Yeka abado, Addis Ababa
Job type: Full-time
Work arrangement: On-site
Application deadline: 2026-11-24
ድርጅታችን የምግብ ፋብሪካውን ለማስፋፋት፣ ማሽነሪዎችን ከቱርክ፣ ከአውሮፓና ከቻይና ለማስመጣት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ማሽነሪዎችን የሚያመርቱ ባለሙያዎችንና ፋብሪካዎችን ለማፈላለግ፣ የብድር ሂደትን ለመከታተል እና ማሽነሪዎችን በትክክል ተክሎ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚችል ብቁና ታማኝ ባለሙያ ይፈልጋል።
የሥራ ድርሻዎች፦ - ለፋብሪካው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችን መለየትና ከቱርክ፣ ከአውሮፓና ከቻይና አምራቾች ማፈላለግ። - በኢትዮጵያ ውስጥ ማሽነሪዎችን ሊያመርቱ የሚችሉ የአካባቢ ባለሙያዎችን፣ የኢንጂነሪንግ ድርጅቶችንና የማሽን ሠሪ ዎርክሾፖችን ማፈላለግና ሥራውን ማስተባበር። - የማሽነሪዎችን ዋጋ፣ ጥራት፣ አቅምና የሥራ ብቃት በማወዳደር የግዥ ምክረ ሐሳብ ማቅረብ። - Bank ጋር የማሽነሪ ብድር ሂደትን መከታተል። - ማሽነሪዎችን በፋብሪካው ማስገጠም፣ ማስፈተሽና ወደ ሥራ ማስገባት።
የሚፈለጉ ብቃቶች፦ - በሜካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ በኢንዱስትሪ ማሽነሪ ወይም በፋብሪካ ማሽነሪ ግዥና ተከላ ላይ ተግባራዊ ልምድ ያለው። - ከውጭ አገር ማሽነሪ የማስመጣትና የኢትዮጵያን የጉምሩክ ሂደት የሚያውቅ። - በአገር ውስጥ የማሽን ሠሪዎችን ማፈላለግና የማምረት ሥራን ማስተባበር የሚችል። - የብድር ሂደቶችን፣ የውጭ አገር አቅራቢዎችንና የፕሮጀክት ሂደቶችን መከታተል የሚችል። - ታማኝ፣ ተግባራዊ፣ ችግር ፈቺና ሥራን ከመጀመሪያ እስከ ፍጻሜ የሚያስፈጽም።
የሥራ ቦታ፦ አዲስ አበባ ማሳሰቢያ፦ በተመሳሳይ ሥራ ላይ ተግባራዊ ልምድ ላላቸው እጩዎች ቅድሚያ ይሰጣል።
Requirements: Mechanical & Electrical Engineering, Machine Operation, Machinery Installation, Machinery Maintenance and Repair, Machine Controls, Machinery Design
Skills and tags: Mechanical & Electrical Engineering, Machine Operation, Machinery Installation, Machinery Maintenance and Repair, Machine Controls, Machinery Design
Apply for this job
Source: Afriwork